Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ ለዓድዋ ድል መታሰቢያ በዓል ለተሽከርካሪ ዝግ የሚደረጉ መንገዶች ይፋ ሆኑ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ ለዓድዋ ድል መታሰቢያ በዓል አከባበር ለተሽከርካሪ ዝግ የሚደረጉ መንገዶች ይፋ ሆነዋል፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ እንዳስታወቀው÷ 128ኛው የዓድዋ ድል መታሰቢያ ክብረ በዓል በአዲስ አበባ ፒያሳ አካባቢ በሚገኘው የዓድዋ ድል መታሰቢያ ይከበራል፡፡

የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ሃይል የካቲት 23 ቀን 2016 ዓ.ም የሚከበረው 128ኛው የዓድዋ ድል መታሰቢያ በዓል በስኬት እንዲከበር ለማስቻል ቅድመ ዝግጅቱን አጠናቆ ወደ ተግባር መግባቱን ማስታወቁ ይታወሳል፡፡

ክብረ በዓሉ በሚከበርበት ዕለት የትራፊክ መጨናነቅ እንዳያጋጥም እና አሽከርካሪዎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑም የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

በዚህም መሰረት፡-

• ከአፍንጮ በር ወደ ቅ/ጊዮርጊስ ቤ/ክርስቲያን፣

• ከሰሜን ሆቴል ወደ ቅ/ጊዮርጊስ ቤ/ክርስቲያን፣

• ከዮሃንስ ቤተ ክርስቲያን ወደ አቡነ ጴጥሮስ፣

• ከአራት መንታ ወደ ጅንአድ፣

• ከይርጋ ሃይሌ የገበያ ማዕከል ወደ አቡነ ጴጥሮስ፣

• ከሃብተ ጊዮርጊስ ድልድይ ወደ ሱማሌ ተራ፣

• ከሱማሌ ተራ ወደ ኤሊያና ሆቴል(ባንኮዲሮማ) መስቀለኛ፣

• ከተክለ ሃይማኖት አደባባይ ወደ ቴዎድሮስ አደባባይ፣

• ከሀገር አስተዳደር መብራት( ኢሚግሬሽን) ወደ ቴዎድሮስ አደባባይ፣

• ከንግድ ማተሚያ ቤት ወደ ቴዎድሮስ አደባባይ፣

• ከአሮጌው ቄራ ወደ ባንኮ ዲሮማ መብራት፣

• ከራስ መኮንን ድልድይ ወደ ደጎል አደባባይ፣

• ከራስ መኮንን ድልድይ ወደ ቅ/ጊዮርጊስ ቤ/ክርስቲያን፣

• ከመቅደላ ሆቴል ወደ ቅ/ጊዮርጊስ ቤ/ክርስቲያን፣

• ከቅ/ጊዮርጊስ ቤ/ክርስቲያን ወደ ቴሌ እና ወደ ቅ/ጊዮርጊስ ቤ/ክርስቲያን ፊት ለፊት ወደሚገኘው አደባባይ የሚወስዱት መንገዶች

የካቲት 23 ቀን 2016 ዓ.ም ከንጋቱ 11 ሰዓት ጀምሮ ለተሽከርካሪ ዝግ ስለሚሆኑ አሽከርካሪዎች ይህንን ተገንዝበው አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ እና የትራፊክ ፖሊሶች የሚጠቁሟቸውን አማራጭ አቅጣጫዎችን በመጠቀም አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርጉ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

በዓሉ በሚከበርበት ዙሪያ ከዋዜማው ከየካቲት 22 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ በዓሉ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ከላይ በተጠቀሱት መንገዶች እና ፕሮግሙ በሚካሄድበት በዓድዋ መታሰቢያ ዙሪያ ተሽከርካሪን ማሳደርም ሆነ ለአጭርም ሆነ ለረጅም ሰዓት ትቶ መሄድ ፈፅሞ የተከለከለ መሆኑንም ተገልጿል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.