Fana: At a Speed of Life!

በ13ኛው የመላ አፍሪካ ጨዋታዎች 149 ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ይሳተፋሉ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በጋና አክራ በሚካሄደው 13ኛው የመላ አፍሪካ ጨዋታዎች 149 ኢትዮጵያውያን አትሌቶች እንደሚሳተፉ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዴዔታ አምባሳደር መስፍን ቸርነት÷የመላ አፍሪካ ጨዋታ አፍሪካውያን ወንድማማቾች የሚገናኙበት ከመሆኑ ባሻገር  የሀገራችን ባህልና ስፖርት የሚተዋውቅበት መድረክ ነው ብለዋል፡፡

መድረኩ  የስፖርቱን ዲፕሎማሲ ለማጠናከር ዋነኛ መሳሪያ መሆኑን የገለፁት ሚኒስትር ዴዔታው÷ ኢትዮጵያ በሁሉም ዘርፍ በአፍሪካም ሆነ በዓለም ደረጃ ያላትን ተሳትፎ ከፍ እንደሚያደርግም ጠቅሰዋል፡፡

በመላ አፍሪካ ጨዋታዎች የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከተሳትፎም በላይ ጥሩ ውጤት ይዞ ይመጣል ተብሎ እንደሚጠበቅ  ተናግረዋል፡፡

13ኛው የመላ አፍሪካ ጨዋታ ከየካቲት 29 እስከ መጋቢት 13 ቀን 2016 ዓ.ም በጋና አክራ  እንደሚካሄድ  የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር  መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.