Fana: At a Speed of Life!

የጋና ኤሌክትሪክ ኩባንያ በዕዳ ምክንያት የፓርላማውን የኃይል አቅርቦት ማቋረጡ ተሰማ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በጋና መንግስት የሚተዳደረው የኤሌክትሪክ ኩባንያ ከ1 ነጥብ 8 ሚሊየን ዶላር በላይ በሆነ ዕዳ ምክንያት ለፓርላማው የሚያደርገውን የኃይል አቅርቦት ማቋረጡ ተሰምቷል።
 
መቋረጡ የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ባቀረቡት ንግግር ላይ የሚካሄደውን ክርክር አውኳል ተብሏል።
 
በሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን የተጋራ ተንቀሳቃሽ ምስል የፓርላማ አባላት ብርሃን በሌለው ክፍል ውስጥ “መብራት ተቋረጠ መብራት ተቋረጠ” በማለት ሲዘምሩ አሳይቷል።
 
ይሁንና ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ በመጠባበቂያ ጀነሬተር የክፍሉ መብራት እንዲመለስ መደረጉን የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል፡፡
 
በድንገት የኃይል መቋረጥ በተከሰተበት ጊዜ አሳንሰር ሲጠቀሙ የነበሩ የፓርላማ አባላት እና የፓርላማ ሠራተኞች እዛው ተዘግቶባቸው መቆየታቸውን የጋና ቴሌቪዥን ዘግቧል።
 
የኤሌክትሪክ ኩባንያው የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር ዊልያም ቦአቴንግ÷ ፓርላማው የክፍያ ማሳወቂያዎችን አክብሮ ባለመቀበሉ ኃይል ለማቋረጥ መገደዳቸውን ተናግረዋል።
 
አክለውም ፓርላማው 57 በመቶ ዕዳውን ከፍሎ ቀሪውን በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ ለመማጠናቀቅ ቃል በመግባቱ በነጋታው የኃይል አቅርቦቱ ወደነበረበት እንደተመለሰለት መግለፃቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።
 
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.