Fana: At a Speed of Life!

17ኛው የሞሐ ግማሽ ማራቶን ውድድር የፊታችን እሑድ ይካሔዳል

አዲስ አበባ፣ የካቲት 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 17ኛው የሞሐ ግማሽ ማራቶን ውድድር የፊታችን እሑድ ከጠዋት 1፡00 ጀምሮ እንደሚካሄድ የአዲስ አበባ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አስታወቀ፡፡

ውድድሩ መነሻው ሰሚት አደባባይ መድረሻው ደግሞ ሰሚት ለስላሳ ፋብሪካ እንደሚሆን ተገልጿል፡፡

በውድድሩ ከ17 ክለቦች የተውጣጡ በ1ኛ ዲቪዚዮን 102 አትሌቶች በ2ኛ ዲቪዚዮን 87 አትሌቶች በድምሩ ነባር አትሌቶችን ጨምሮ 279 ተወዳዳሪዎች ይካፈሉበታል ተብሏል፡፡

ውድደሩ የአዲስ አበባ ከተማ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ከሞሐ ለስላሳ መጠጦች ኢንዱስትሪ አክስዮን ማሕበር ጋር በመተባበር የሚያዘጋጀው መሆኑ ተመላክቷል፡፡

በ2016 የሞሐ ግማሽ ማራቶን ውድድር ከ1ኛ እስከ 5ኛ የሚወጡ አትሌቶች የገንዘብ ሽልማት ይበረከታል ።

በወርቅነህ ጋሻሁን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.