Fana: At a Speed of Life!

በዓለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮና ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ማጣሪያውን በቀዳሚነት አለፉ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በግላስጎ የዓለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮና የ800 ሜትር ማጣሪያ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በተለያየ ምድብ ማጣሪያውን አልፈዋል፡፡

ከምድብ አንድ አትሌት ሀብታም ዓለሙ እንዲሁም ከምድብ አራት ጽጌ ዱጉማ 2 ደቂቃ ከ50 ማይክሮ ሰከንድ በመግባት ውድድሩን በቀዳሚነት በማጠናቀቅ ወደ ቀጣዩ ዙር አልፈዋል፡፡

በሌላ በኩል ምሽት 1፡00 ሠዓት ላይ በሚካሄደው የሴቶች 1 ሺህ 500 ሜትር ማጣሪያ ውድድር÷ አትሌት ፍሬወይኒ ኃይሉ፣ ድርቤ ወልተጂ እና ብርቄ ኃየሎም ይጠበቃሉ፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.