Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ታምርት 2016 ዓለም ዓቀፍ ኤክስፖ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር እየተካሄደ ነው

 

አዲስ አበባ፣ የካቲት 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ታምርት 2016 ዓለም ዓቀፍ ኤክስፖ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር እየተካሄደ ይገኛል፡፡

በመርሃ ግብሩ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል፣ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች እንዲሁም ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በአዲስ አበባ እየተካሄደ ይገኛል።

የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ መላኩ አለበል በወቅቱ እንዳሉት፤ የኢትዮጵያ ታምርት የኢኮኖሚ ነፃነትና የሀገር ሉዓላዊነት በውስጡ ያካተተ ንቅናቄ ነው ብለዋል።

ንቅናቄው በኢትዮጵያ የተሰሩትን ማስተዋወቅ፣ አምራችና የፋይናንስ ተቋማት፣ የዘርፉ ተዋናዮች መካከል ትብብርን ለመፍጠር ያለመ መሆኑን ጠቁመዋል።

በባለፈው ዓመት የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ 450 አምራቾች የተሳተፉበት፣ 25 ሚዲያዎች ሽፋን የሰጡበት፣ 53 ሺህ በላይ ጎብኝዎች የታደሙበት፣ 125 የንግድ ስምምነቶች የተፈረሙበት እንዲሁም 25 ቢሊዮን ብር ግብይት የተከናወነበት መሆኑን ገልፀዋል።

የኢትዮጵያ ታምርት 2016 ኤክስፖ የገበያ ትስስርን ለመፍጠር፣ አምራችና የፋይናንስ ተቋማትን ለማገናኘት፣ ዓለም ዓቀፍ ተጠቃሚነትን ለማሳደግ፣ በዘርፉ ያሉ ማነቆዎችን ለመፍታት፣ የግል ባለሃብቱን ማበረታታት እንዲሁም በዘርፉ ተዋናዮች መካከል ትስስርን ለመፍጠር በሚያስችል መልኩ እንደሚካሄድ ጠቁመዋል።

በኤክስፖው ኢንዱስትሪዎች የገበያ ትስስር የሚፈጥሩበት፣ ጥቃቅን አምራቾች ምርቶቻቸውን የሚሸጡበትና ሸማቾች የሚገበያዩበት፣ የፓናል ውይይቶች የሚደረጉበት፣ ካለፉት ልምድ የሚወሰድበትና ያልተፈቱ ችግሮች መፍትሄ ለማበጀት የሚሰራበት መሆኑን ሚኒስትሩ አመላክተዋል።

በመራኦል ከድር

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.