Fana: At a Speed of Life!

የዓድዋ ድል በዓል በዛሬው ዕለት በተለያዩ መርሐ ግብሮች ይከበራል

አዲስ አበባ፣ የካቲት 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 128ኛው የዓድዋ ድል በዓል በዛሬው ዕለት በተለያዩ መርሐ ግብሮች በመላው ኢትዮጵያ ተከብሮ ይውላል።

የዓድዋ ድል መታሰቢያ በዓል አከባበርን የሀገር መከላከያ ሰራዊት የሚያስተባብረው ሲሆን÷ ከፍተኛ በሆነ ሀገራዊ ንቅናቄ በድምቀት ለማክበር ካለፈው ዓመት የተገኙ ልምዶች ተወስደው በተለየ ሁኔታ ለማክበር አስፈላጊ ቅድመ ዝግጅት ተደርጓል።

የሰራዊቱን ድሎችና አኩሪ ገጽታ በሚያጎላ መልኩ ድሉን ለመዘከር በተገነባው ግዙፉ የዓድዋ ድል መታሰቢያ ውስጥ በዓሉ ይከበራል።

ከዚህ በተጨማሪ በሀገር አቀፍ ደረጃ በሁሉም ክልሎች፣ በከተማ አስተዳደሮች፣ በተቋማት፣ በመላው ዓለም በሚገኙ ኤምባሲዎች እና ቆንስላዎች በዓሉ በድምቀት የሚከበር ይሆናል።

በዓድዋ ድል በዓል የተለያዩ ታሪካዊ ወታደራዊ ትዕይንቶች፣ ጥበባዊ ክዋኔዎች እና ሌሎችም መርሐ ግብሮች እንደሚከናወኑ ተነግሯል።

በዚህም ወታደራዊ የሰልፍ ትርዒትን ጨምሮ ድሉን የሚያስታውሱ ልዩ ልዩ ዝግጅቶች እንደሚቀርቡም ተጠቁሟል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.