Fana: At a Speed of Life!

128ኛው የዓድዋ ድል በድምቀት እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 128ኛው የዓድዋ ድል በዓል በአዲስ አበባ ፒያሣ በተገነባው የዓድዋ ድል መታሰቢያ በድምቀት እየተከበረ ነው፡፡

በአከባበሩ ላይም÷ የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ አገኘሁ ተሻገር፣ የፌደራል እና የክልል ከፍተኛ የመንግሥት ሥራ ኃላፊዎች፣ የመከላከያ ሠራዊት አባላትና አመራሮች፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

አፈጉባዔ አገኘሁ እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት ሥራ ኃላፊዎች በዳግማዊ አጼ ምኒልክ ሐውልት እና በዓድዋ ድል መታሰቢያ በሚገኘው ፓን አፍሪካኒዝም ሐውልት ሥር የአበባ ጉንጉን አስቀምጠዋል፡፡

ለሀገራቸው ነጻነት መስዋዕትነት ለከፈሉ ጀግኞች ዓርበኞችም የሕሊና ጸሎት ተደርጓል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.