Fana: At a Speed of Life!

በሶማሊያ አትሚስ ጥላ ስር የሚገኘው ሴክተር 3 የዓድዋ ድል በዓልን አከበረ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሶማሊያ አትሚስ ጥላ ስር የሚገኘው ሴክተር ሦስት 128ኛውን የዓድዋ ድል በዓል በተለያዩ ዝግጅቶች በድምቀት አከበረ፡፡

የሴክተሩ ዋና አዛዥ ብ/ጀኔራል በስፋት ፈንቴ በወቅቱ ባስተላለፉት መልዕክት÷ ዓድዋ የኢትዮጵያ ዓርበኞች ጥምረት፤ የጥቁር ሕዝቦች አሸናፊነት ችቦ ለኳሽ፤ የአፍሪካዊያን ኩራት እና የነፃነት ምልክት ነው ብለዋል።

በሀገር ወዳድ ጀግኖች የመዋጋት አቅም፣ የውጊያ ጥበብ እና ብልሃት እንደ አንድ ሰው በማሰብ በጦር በጎራዴ ሀገር ያቀኑ የአያት ቅድመ አያቶቻችን ተኪ በመሆናችንም ኩራት ይሰማናል ነው ያሉት፡፡

በተመሳሳይ በኢትዮጵያ ወታደራዊ አካዳሚ በሁርሶ እጩ መኮንኖች ትምህርት ቤት 128ኛው የዓድዋ ድል ተከብሯል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.