Fana: At a Speed of Life!

80 በመቶ የኢንተርኔት ፍሰትን በሀገር ውስጥ ለማድረግ እየተሠራ መሆኑ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 80 በመቶ የኢንተርኔት ፍሰቱን በሀገር ውስጥ በማድረግ ይወጣ የነበረን 60 ሚሊየን ዶላር ለማዳን እየሠራ መሆኑን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ሚኒስቴሩ ባዘጋጀው የኢትዮጵያን የዲጂታል አቅሞች ማሳወቂያ ሥነ-ሥርዓት ላይ÷ የኢንተርኔት ስም መዝጋቢ፣ የሠዓት ሥርዓት፣ ኢ-ሜል፣ የዶሜን አድራሻ አፈላላጊ፣ የሀገራትን የዶሜን ስም መዝጋቢ፣ የቀጣዩ ትውልድ የኢንተርንልት ፕሮቶኮል፣ የዶሜን ስም ትክክለኛነት ማረጋገጫ  የተሰኙ የዲጂታል ፕሮጀክቶች ቀርበዋል፡፡

ፕሮጀክቶቹ ሲጠናቀቁም 80 በመቶ የኢንተርኔት ትራፊክ ፍሰትን በሀገር ውስጥ በማድረግ 60 ሚሊየን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ማዳን ያስችላል መባሉን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴዔታ ይሽሩን ዓለማየሁ (ዶ/ር) ሀገራዊ የዲጂታል አቅሞቻችንን አሟጥጠን በመጠቀም የኢትዮጵያን የዲጂታል ውጥን እውን እናደርጋለን ብለዋል።

በሚኒስቴሩ ስር አየተተገበረ ያለው ፕሮጀክት ሲጠናቀቅም የኢንተርኔት ፍጥነትን 60 በመቶ እንደሚያሳድግ ጠቅሰዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.