Fana: At a Speed of Life!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በልደታ ክ/ከተማ የመኖሪያ ቤት ግንባታ አስጀመሩ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በልደታ ክ/ከተማ ከ300 በላይ ክፍሎችን የሚይዝ ባለ ዘጠኝ ወለል የመኖሪያ ቤት ግንባታን አስጀምረዋል፡፡

ከንቲባዋ ግንባታውን ባስጀመሩበት ወቅት÷ በአዲስ አበባ ያለውን የመኖሪያ ቤት ችግር ለመፍታት በትኩረት እየሰራን ነው ብለዋል።

የቤት ግንባታው ለዓድዋ ድል መታሰቢያ ልማት ለተነሱ ዜጎችና በልማት ለሚነሱ ዜጎች መሆኑን ጠቅሰው÷ ግንባታው ሲጠናቀቅም ለከተማዋ የገፅታ ግንባታ ከማላበስ ባለፈ የዜጎችን ህይወትም ያዘምናል ነው ያሉት፡፡

ግንባታውን በአጭር ጊዜ ውስጥ እንደሚጠናቀቅም ገልጸዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.