Fana: At a Speed of Life!

በምስራቅ ጉጂና ምስራቅ ቦረና ዞኖች የሚንቀሳቀሰው የአሸባሪው ሸኔ ክንፍ ከፍተኛ አመራሮች እጅ እየሰጡ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ጉጂ እና ምስራቅ ቦረና ዞን እየተንቀሳቀሰ የሚገኘው የአሸባሪው ሸኔ ክንፍ አባላትና ከፍተኛ የሸኔ አመራሮች ለመከላከያ ሠራዊቱ እጅ እየሰጡ መሆኑ ተገለጸ።

በጉጂ ዞን የቡድኑ ሎጅስቲክስ እና ፖለቲካ ዘርፍ ሃላፊ የነበረው ገመዳ ዱጎ በቅጽል ስሙ ሎንግ እየተባለ የሚጠራው ግለሰብ በቅርቡ እጅ መስጠቱን ይታወሳል።

ይህንን ተከትሎ የሻለቃ መረጃና ፖለቲካ ዘርፍ ሃላፊ ዱቤ በሪሶ ወይም አባጨብስ የተባለውን ግለሰብ ጨምሮ ሌሎች ሰባት የቡድኑ አመራርና አባላት ከሠሞኑ እጅ ሰጥተዋል።

ቡድኑ ከፖለቲካ አላማ ይልቅ ህዝብ የማሰቃየት እና የመዝረፍ ተግባር ላይ በመሰማራቱ ከቡድኑ ጋር ያለውን ግንኙነት በማቋረጥ ለሠራዊቱ እጅ መሰጠታቸው ተገልጿል።

በደቡብ ዕዝ የኮር አዛዥ ኮሎኔል ግርማ አየለ በምስራቅ ጉጂ እና ምስራቅ ቦረና ዞኖች እየተወሰደ ባለው የተቀናጀ ኦፕሬሽን ቡድኑ ትርጉም ወደ ማይሰጥበት ደረጃ እየወረደ እንደሚገኘ አመልክተዋል።

የቡድኑን እንቅስቃሴ ለመግታት እየተደረገ ባለው ጥረት ህብረተሰቡ በተለያየ መንገድ ከሠራዊቱ ጎን በመሆን የድርሻውን እየተወጣ እንደሚገኝም መናገራቸውን ከኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት የማኅበራዊ ትስስር ገፅ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

በአካባቢው መንግስታዊ አገልግሎቶችን ጨምሮ የልማት ስራዎች ያለምንም መስተጓጐል በመከናወን ላይ እንደሚገኙም ጠቁመዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.