Fana: At a Speed of Life!

የሐረሪ ክልል ካቢኔ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ውሳኔ አሳለፈ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሐረሪ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል።

ምክር ቤቱ በሐረር ከተማ ማዘጋጃ ቤት የከተማ ተቋማዊ እና የመሰረተ ልማት ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽ/ቤት በ2016 በጀት ዓመት በተዘጋጀው የ”ሲ አይ ፒ” እቅድ እና የከተማዋ ማዘጋጃ ቤት የገቢ ርዕሶችና ታሪፍ ማሻሻያ ረቂቅ ደንብ ላይ ተወያይቷል።

በዚህም በከተማ ተቋማዊና መሰረተ ልማት ማስፋፊያ ፕሮግራም የ2016 በጀት ዓመት ካፒታል ኢንቨስትመንት እቅድን መርምሮ አጽድቋል።

በ”ሲ አይ ፒ” እቅድ ከባለፈው በጀት ዓመት የዞሩ 12 ፕሮጀክቶች እና በ2016 ለማከናወን የተያዙ አዳዲስ 29 ፕሮጀክቶችን ማስፈጸሚያ የቀረበለትን 242 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር በጀትም መርምሮ አጽድቋል።

መስተዳደር ምክር ቤቱ የሐረር ከተማ ማዘጋጃ ቤት የገቢ ርዕሶችና ታሪፍ ማሻሻያ ረቂቅ ደንብ ላይ ከተወያየ በኋላ ከዛሬ ጀምሮ ሥራ ላይ እንዲውል ወስኗል፡፡

በተጨማሪም ምክር ቤቱ በሌሎች አጀንዳዎች ዙሪያ ተወያይቶ ውሳኔ ማሳለፉን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.