Fana: At a Speed of Life!

ሕዝቡና ሠራዊቱ ከተናበበ ጸረ-ሰላም ቡድን ሽብር እየፈጠረ የሚቆይበት ዕድሜ አይኖረውም – ሌ/ጄ ዘውዱ በላይ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሕዝቡና ሠራዊቱ ተናቦ ከሰራ ጸረ-ሰላም ቡድን ሽብር እየፈጠረ የሚቆይበት ዕድሜ አይኖረውም ሲሉ የማዕከላዊ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጀኔራል ዘውዱ በላይ ገለጹ፡፡

የማዕከላዊ ዕዝ ከፍተኛ አመራሮች ከምስራቅ ወለጋ ዞን ወረዳዎች ከተወጣጡ የማህበረሰብ ክፍሎች ጋር የሰላም ኮንፈረንስ አካሂደዋል።

የማዕከላዊ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጀኔራል ዘውዱ በላይ እንዳሉት ፥ የሚያጋጥሙ ችግሮች በውይይት ለመፍታት ሕዝቡና ሠራዊቱ ተናቦ መስራት አለበት፡፡

ይህ ከሆነም ለሰላም እንቅፋት የሚሆን፣ ነፃነቱን የሚገፍ፣ በኃይል የሚፈታተነውና የልማቱ እንቅፋት የሆነ ፀረ-ሰላም ቡድን ሽብር እየፈጠረ የሚቆይበት ዕድሜ እንደማይኖረው አስረድተዋል።

አክለውም ፥ ወታደሩ የአመለካከት ልዩነት ያለውን ማንኛውንም ኃይል የመቃወም ዓላማ እንደሌለው ተናግረውአስገንዝበዋል፡፡

ሆኖም የትኛውም የፓለቲካ ኃይል ልዩነቱን የሚያራምደው ነፍጥ አንግቦ ከሆነ ለሀገር ደህንነትና ለሕዝቦች ሰላም ሲል ሠራዊቱ ሳይፈልግ ወደ ጦርነት ለመግባት ይገደዳል ብለዋል፡፡

ይህ እንዳይሆን ልዩነቶችን በሰላማዊ መንገድ እንፍታ ሲሉም ነው ጥሪ ያቀረቡት፡፡

የምስራቅ ወለጋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዋጋሪ ነገራ በበኩላቸው ፥ አሸባሪው ሸኔ በዞኑ በሚፈፅመው ሽብር ሕዝቡ ለሰላም እጦት ተዳርጎ ቆይቷል ፤ ሆኖም መከላከያ ሠራዊቱ በወሰደው እርምጃ አንፃራዊ ሰላም ማግኘት ተችሏል ብለዋል።

ማህበረሰቡ ለመከላከያ ሠራዊት መረጃ በማቀበልና ጠላትን አጋልጦ በመስጠት የበኩሉን ኃላፊነት እንዲወጣ ጥሪ መቅረቡንም የሠራዊቱ ማህበራዊ ትስስር ገጽ መረጃ ያመላክታል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.