Fana: At a Speed of Life!

ኤክስ በአውሮፓ ህብረት አዲስ ገደቦች ሊጣሉበት እንደሚችል ተመላከተ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኤክስ (የቀድሞው ትዊተር) የተሰኘው ማህበራዊ ትስስር ገጽ በአውሮፓ ህብረት አዲስ ገደቦች ሊጣሉበት እንደሚችል ተመላክቷል፡፡
 
የአውሮፓ ኮሚሽን÷ ማህበራዊ ትስስር ገፁ በዲጂታል ገበያ ህግ መሰረት ከተከለከሉ ሥርዓቶች ውስጥ ሊመደብ እንደሚችል ካስታወቀ በኋላ በአውሮፓ ህብረት ጥብቅ መመሪያዎችን ለመከተል ሊገደድ ይችላል ተብሏል፡፡
 
ኩባንያዎች÷ የመፈለጊያ ቋቶችን፣ የመተግበሪያ መገኛዎችን እና የመልእክት አገልግሎቶችን ጨምሮ የገጹን ዋና አገልግሎቶች ተግባራዊ የሚያደርጉ ከሆነ ለተጨማሪ ደንቦች ተገዢ ሊሆኑ እንደሚችሉ የአውሮፓ ኮሚሽን አብራርቷል፡፡
 
ይህም ማለት ከ45 ሚሊየን በላይ ወርሃዊ ንቁ ተጠቃሚዎች፣ ከ10 ሺህ በላይ የንግድ ተጠቃሚዎች አሊያም ደግሞ ከ75 ቢሊየን ዩሮ በላይ የገበያ ድርሻ ሊኖራቸው እንደሚገባ ተመላክቷል።
 
በአውሮፓ ኮሚሽን ድረ ገጽ በፈረንጆቹ መጋቢት 1 ቀን 2024 ላይ በወጣው ማስታወቂያ መሰረት ኤክስ፣ እንዲሁም የጉዞ ድረ ገፆች እና የቲክቶክ ባለቤት ባይትዳንስ አገልግሎታቸው የዲጂታል ገበያ ህግ መስፈርቶችን የሚያሟላ እንደሆነ የሚገልፅ ማሳወቂያዎችን ማቅረባቸው ተገልጿል።
 
ኮሚሽኑ አሁን ሦስቱን ኩባንያዎች “ከተከለከሉ ሥርዓቶች” ውስጥ ለመመደብ ወይም ላለመመደብ 45 ቀናት እንዳሉት አርቲ ዘግቧል።
 
መስፈርቱን የሚያሟሉ ከሆነ ደግሞ የዲጂታል ገበያ ህግ መስፈርቶች ለማክበር ስድስት ወራት እንደሚኖራቸው ተመላክቷል።
 
እንደ አፕል፣ ሜታ፣ አማዞን፣ ማይክሮሶፍት እና አልፋቤት ያሉ ኩባንያዎች የክልከላ ስያሜ ከተቀበሉ መካከል እንደሚካተቱም ተጠቁሟል።
 
ክልከላ የተጣለባቸው ኩባንያዎች ገፆቻቸው የሚያመነጯቸውን መረጃዎች ለንግድ ተጠቃሚዎች እንዲደርሳቸው ለማስቻል እና ከደንበኞቻቸው ጋር ውል ለመፈፀም የሦስተኛ ወገን ፍቃድ እንደሚያስፈልጋቸው ተጠቁሟል፡፡
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.