Fana: At a Speed of Life!

አራት ኪሎ የሚገኙት የእግረኛ መሸጋገሪያ ድልድዮችን የማንሳት ሥራ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አራት ኪሎ አካባቢ የሚገኙትን ሁለት የእግረኛ መሸጋገሪያ የብረት ድልድዮችን የማንሳት ሥራ እየተከናወነ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን አስታወቀ፡፡

ድልድዮቹን የማንሳት ሥራው እየተከናወነ የሚገኘው የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ካቢኔ በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች ዓለም አቀፍ የስማርት ሲቲ ስታንዳርድን የሚያሟሉ አዳዲስ አራት የመንገድ ኮሪደሮች ግንባታ እንዲከናወን ውሳኔ ማሳለፉን ተከትሎ ነው ተብሏል፡፡

የብረት ድልድዮችን የማንሳት ሥራም በሁለት ቀናት ውስጥ ይጠናቀቃል መባሉን ከባለስልጣኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ሥራው እስከሚጠናቀቅም የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይፈጠር አሽከርካሪዎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ ተጠይቀዋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ቀደም ብሎ “አራት ኪሎ ዳግማዊ ምኒልክ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አጠገብ የሚገኘው የእግረኞች መሸጋገሪያ ድልድይ ጉዳት ደርሶበታል” በሚል ያሰራጨው ዘገባ ስህተት መሆኑን እየገለጸ ለዚህም ይቅርታ ይጠይቃል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.