Fana: At a Speed of Life!

የሳይበር ደህንነትና የዲጂታል ሽግግር ጉባኤ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሳይበር ደህንነትና የዲጂታል ሽግግር ጉባኤ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል፡፡

ጉባኤው የኢትዮጵያን የሳይበር ደህንነትና ሉዓላዊነት ለማስጠበቅና ሀገራዊ የሳይበር ሥነ ምህዳር ማጠናከር ላይ በስፋት ለመምከር እንደተዘጋጀ ተጠቁሟል፡፡

ለሁለት ቀናት በሚካሄደው ጉባኤ የሳይበር ደህንነት፣ የሳይበር ህግ እና ተያያዥ ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ ከ12 በላይ ጥናታዊ ፅሑፎች ቀርበው ውይይት እንደሚደረግባቸውም ተገልጿል።

ጉባኤው ማህበረሰቡ ስለሳይበር ደህንነት ግንዛቤ እንዲኖረው የማድረግ ዓላማ እንዳለውም ተጠቅሷል፡፡

በጉባኤው የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ትዕግሥት ሃሚድ፣ የኢትዮጵያ ሳይበር ደህንነት ማህበር ፕሬዚዳንት ብርሃኑ በየነ (ዶ/ር) እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው የዘርፉ አመራሮችና ተመራማሪዎች ተገኝተዋል።

መድረኩን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ከኢትዮጵያ ሳይበር ደህንነት ማህበር ጋር እንዳዘጋጁት ኢዜአ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.