Fana: At a Speed of Life!

በህዳሴ ግድብና በአባይ ወንዝ አጠቃቀም ላይ ያተኮረ ውይይት በባህር ዳር እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 29 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በባህርዳር ዩኒቨርስቲ በታላቁ ህዳሴ ግድብና በአባይ ወንዝ ዙሪያ የምሁራን ውይይት እየተካሄደ ነው።

በውይይቱ የዩኒቨርስቲው ምሁራን ፣ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዋና የህግ አማካሪ አቶ መርኸፅድ መኮንንና ሌሎች አመራሮች ተገኝተዋል።

ውይይቱም በታላቁ ህዳሴ ግድብና በአባይ ወንዝ ዙሪያ ታሪካዊ፣ፖለቲካዊ እና ህጋዊ የውሃ ሀብት አጠቃቀምና የዲፕሎማሲ ግንኙነት ላይ ያተኮረ ነው።

የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ በህዳሴው ግድብ ዙሪያ ለሚደረጉ ድርድሮች ለተደራዳሪዎች አማራጭ ማቅርብ፣ የድርድሩን እንደምታ ለህዝብ ማሣወቅና የቀደሙ ስህተቶችን አርሞ የኢትዮጵያ ጥቅም ማስጠበቅ ላይ ያለመ ውይይት በመካሄድ ላይ ይገኛል።

በናትናኤል ጥጋቡ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.