Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ወ/ሮ አዳነች አበቤ ቴምፕል ኦፍ ጎድ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ጎዳና ላይ የወደቁ ወገኖችን የመደገፍ ስራን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 30፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ወ/ሮ አዳነች አበቤ ቴምፕል ኦፍ ጎድ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ጎዳና ላይ የወደቁ ወገኖችን የመደገፍ ስራን ጎበኙ፡፡

ጠቅላይ ዐቃቤ ወ/ሮ አዳነች አበቤ በፌስ ቡክ ገፃቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ ለመረዳዳት የግድ የበጎ አድራጊ ድርጅት ፣ሰራተኛ መሆን አያስፈልግም ነው ያሉት።

ጎዳና ላይ የወደቁ 250 ወገኖች ከኮቪድ 19 ወረርሽኝ የመከላከል እና የመደገፍ ሰራን ስጦታ በመያዝ መጎብኘታቸውን እና ማበረታታቸውን ገልፀዋል።

ጠቅላይ ዐቃቤ ወ/ሮ አዳነች ይህ በጎ እና የሚበረታታ ተግባር ለሁላችንም ምሳሌ መሆን ይችላል በማለት ያሳሰቡ ሲሆን ከራስ በላይ ለሌሎችም ለመኖር ተነሳሽነቱ ካለን በእርግጥ እንችላለንም ነው ያሉት።

በቀጣይም የእነዚህን ወገኖቻችንን ህይወት በዘላቂነት ለመቀየር በሚደረገው ርብርብ ዉስጥ ሁላችንም ተባብረን መስራት ይጠበቅብናል ሲሉም ተናግረዋል፡፡

ቴምፕል ኦፍ ጎድ ቤተ ክርስቲያን እነዚህን ወገኖች ከጎዳና ላይ አንስተው መርዳት ከጀመሩ 3 ወር ሆኗቸዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.