Fana: At a Speed of Life!

በወላይታ ዞን አራት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተመረቁ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 30፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በወላይታ ዞን በሊንክ ኮሚዩኒቲ ዲቪሎፕመንት ከ70 ሚሊየን ብር በላይ ወጭ የተገነቡ አራት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተመረቁ ።
ትምሀርት ቤቶች ደረጃቸውን በጠበቀ መልኩ የተገነቡ ሲሆን፥ የሴቶችን ችግር በእጅጉ ሊቀርፍ የሚችል እንደሆነ በኢትዮጵያ የሊንክ ኮሚዩኒቲ ዲቪሎፕመንት ዳይሬክተር አቶ ታደሠ ገመዳ ተናግረዋል ።

የሴት ልጆችን የትምህርት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በቀጣይም የሚሰራ መሆኑን በመግለፅ በአጠቃላይ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን ተጠቃሚ ያደርጋል ነው የተባለው ።

ትምህርት ቤቶቹ በዳሞታ ወይዴ፣ በዳሞታ ፑላሳ፣ በዳሞታ ሶሬ እና በክንዶ ኮይሻ ወረዳዎች የተገነቡ ሲሆን ፥ትላንት ከተመረቁት ሶስት ትምህርት ቤቶች ውጭ አራተኛው ትምህርት ቤት ቀደም ብሎ ስራ መጀመሩን ጨምረው ገልፀዋል ።

ተቋሙ የሴቶችን ተፅእኖ ሊቀርፉ በሚችሉ ጉዳዮች ላይ እየሰራ ይገኛል ያሉ ሲሆን፥ የትምህርት ዘርፍ ዋነኛ ትኩረቱ ነው ብለዋል።

ከደቡብ ክልል ውጪ በአፋር፣ ሶማሌ፣ ጋምቤላ እና ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች ላይ በመስራት ላይ ይገኛል ተብሏል ።

የደቡብ ክልል ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶክተር ጌታሁን ጋረደው በበኩላቸው ተቋሙን በማመስገን ትምህርት የሁሉም ነገር መሠረት በመሆኑ በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋ።

ህዝቡም ከትምህርት ተቋማት ጋር ያለውን ትስስር አጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል ።

በብርሃኑ በጋሻው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.