Fana: At a Speed of Life!

በአዲስ አበባ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ1 ሺህ 500 በልጧል

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 30 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ1 ሺህ 500 በልጧል፡፡

በዛሬው እለት የኮሮና ቫይረስ ከተገኘባቸው 86 ሰዎች ውስጥ 66 ሰዎች ከአዲስ አበባ ሲሆኑ በአጠቃላይም በመዲናዋ 1ሺህ 510 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

ይህንን ተከትሎም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ በከተማዋ የቫይረሱ ስርጭት በክፍለ ከተሞች ደረጃ የሚያመላክት መረጃ አውጥቷል።

በዚህም በአዲስ አበባ በ24 ሰዓት ውስጥ ቫይረሱ ከተገኘባቸው 66 ሰዎች መካከል 18 ሰዎች ከአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፥ 9 ሰዎች ደግሞ ቦሌ ክፍለ ከተማ ይገኛሉ።

እንዲሁም ጉለሌ 6 ፣ኮልፌ ቀራኒዮ 5 እና ቂርቆስ ክፍለ ከተማ 6 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል፡፡

በአጠቃላይም እስከአሁን በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ 410 ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ ጉለሌ 210 እንዲሁም ልደታ ክፍለ ከተማ 196 ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.