Fana: At a Speed of Life!

ጥቂት ስለአዕምሮ እድገት ውስንነት

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዕምሮ እድገት ውስንነት አንድ ሰው ተጨማሪ ክሮሞዞም ሲኖረው የሚከሰት ነው፡፡

ዛሬ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚከበረው የአዕምሮ እድገት ውስንነት፥ የአካል እና የአዕምሮ እድገት መዘግየት እና የአካል ጉዳትን እንደሚያስከትል የዘርፉ ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡

ክሮሞዞምች በሰውነት ውስጥ ጥቃቅን የዘር “ጥቅሎች” ሲሆኑ፥ በእርግዝና ወቅት እና ከተወለደ በኋላ የሕፃኑ አካል እንዴት እንደሚያድግና እንደሚሰራ ይወስናሉ፡፡

በዚህ ህመም የተያዙ ህጻናት የሚያጋጥማቸው የአካል ጉዳት የዕድሜ ልክ እንደሆኑና ለሞትም የሚዳርግ ሊሆን እንደሚችል ይነገራል፡፡

ይሁን እንጂ የአዕምሮ እድገት ውስንነት ያለባቸው ሰዎች ጤናማ እና አርኪ ሕይወት መኖር እንደሚችሉም ይነሳል፡፡

በእርግዝና ወቅት የአዕምሮ እድገት ውስንነት በህክምና ሲታይ ሊገመት የሚችል ቢሆንም በእርግዝና ወቅት እናት የሚሰማት የተለየ ነገር እንደማይኖርም ነው የሚነገረው፡፡

ሆኖም ልጁ ከተወለደ በኋላ የአዕምሮ እድገት ውስንነት ምልክትን ሊያሳይ ይችላል፡፡ እነዚህም፡-
• ጠፍጣፋ የፊት ገጽታዎች፣
• ትንሽ ጭንቅላት እና ጆሮዎች ወይም ያልተለመደ ቅርጽ ያላቸው ጆሮዎች፣
• አጭር አንገት፣
• የሚጎተት ምላስ፣
• ወደ ላይ ማየት፣
• ደካማ ጡንቻና የመሳሰሉት ይጠቀሳሉ፡፡
የአዕምሮ እድገት ውስንነት ያለበት ህጻን በአማካይ መጠን ሊወለድ የሚችል ቢሆንም፥ ልጁ ህመሙ ከሌለበት ጋር ሲነጻጸር አነስተኛ እድገት እንደሚኖረው የህክምና ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡

በዚህም የአዕምሮ እድገት ውስንነት ያለባቸው ሰዎች ብዙውን ጊዜ በተወሰነ ደረጃ የዕድገት እክል ያለባቸው እንደሆኑ የኸልዝላይን መረጃ ያመላክታል፡፡

የአዕምሮ እድገት ውስንነት ባለባቸው ሰዎች ላይ ብዙውን ጊዜ የጤና እክሎች የተጋለጡ ናቸው። ከእነዚህም መካከል፡-

• የልብ ችግር፣
• የመስማት ችግር፣
• ደካማ እይታ፣
• የዓይን ሞራ ግርዶሽ (ደመናማ ዓይኖች)፣
• የመቀመጫ አፈጣጠር ችግር፣
• የደም ካንሰር (ሉኪሚያ)፣
• ሥር የሰደደ የሆድ ድርቀት ህመም፣
• በእንቅልፍ ጊዜ የመተንፈስ ችግር፣
• የማሰብ እና የማስታወስ ችግሮች፣
• ዝቅተኛ የታይሮይድ ተግባር፣
• ከመጠን ያለፈ ውፍረት፣
• ዘግይቶ የጥርስ እድገት (በማኘክ ላይ ችግር ይፈጥራል)፣
• ከጊዜ በኋላ የአልዛይመር በሽታና የመሳሰሉት ይጠቀሳሉ፡፡

በተጨማሪም የአዕምሮ እድገት ውስንነት ያለባቸው ሰዎች ለኢንፌክሽን የተጋለጡ እንደሆነ የሚነሳ ሲሆን ፥ የመተንፈሻ አካላት፣ የሽንት ቱቦዎች እና የቆዳ ኢንፌክሽን የማጋጠም እድሉ ከፍተኛ መሆኑ ይገለጻል፡፡

የአዕምሮ እድገት ውስንነት መድሃኒት የሌለው ቢሆንም የተለያዩ ድጋፍና የትምህርት እገዛዎች ከተደረጉላቸው፣ ባለሙያዎችን በየጊዜው ካማከሩና ክትትልም ካደረጉ ከራሳቸው አልፈው ለሌሎች አስተዋጽዖ የሚያደርጉ ዜጎች ሊሆኑ እንደሚችሉም የዘርፉ ባለሙያዎች ያስገነዝባሉ፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.