Fana: At a Speed of Life!

የፀሐይ አውሮፕላን ሀገር ቤት መመለስ ለአቪዬሽን ባለሙያዎች የሞራል ስንቅ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የፀሐይ አውሮፕላን ወደ ሀገር ቤት መመለስ ለዘመኑ የአቪዬሽን ባለሙያዎች ትልቅ የሞራል ስንቅ መሆኑን የኢትዮጵያ አየር ኅይል አመራርና አባላት ገለጹ።

የኢትዮጵያ አየር ኅይል አመራርና አባላት የአድዋ ድል መታሰቢያን ጎብኝተዋል፡፡

የኢትዮጵያ አየር ኅይል አመራርና አባላት በጉብኝቱ ወቅት እንደገለጹት÷የኢትዮጵያ አየር ሃይል ሀገር የማዘመን እና የቴክኖሎጂና ፈጠራ ልህቀትን የሚያበረታታ መሆኑን ተናግረዋል።

የፀሃይ ሀገር ቤት መግባትም ለኢትዮጵያ ጉልህ የታሪክ አሻራና ለዘመኑ የአቪዬሽን ባለሙያዎች ደግሞ ትልቅ የሞራል ስንቅ መሆኑን ገልጸዋል።

የአየር ኅይል አባላቱም ዘመኑ ባፈራቸው ቴክኖሎጂዎች በመመራት በተሻለ ቁመና እና ሞራል እንዲሰሩ የሚያነሳሳ ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

“ፀሐይ “ወይም “ኢትዮጵያ አንድ” የሚል ስያሜ የተሰጣት ይህች ጥንታዊት አውሮፕላን በኢትዮጵያውያን የተሰራች ስትሆን ጠላት አዲስ አበባን ሲቆጣጠር ወደ ሮም መወሰዷ ይታወቃል።

በተደረገ ዲፕሚሲያዊ ጥረትም ከ88 ዓመታት በኋላ አውሮፕላኗ ወደ ሀገር ቤት ተመልሳ በአድዋ ድል መታሰቢያ በክብር ተቀምጣ ትገኛለች።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.