Fana: At a Speed of Life!

የሩሲያ ኖቭግሮድ ግዛት ከፍተኛ ኃላፊዎች በኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ለመስራት ያላቸውን ፍላጎት አሳዩ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሩሲያ የኖቭግሮድ ግዛት ከፍተኛ ኃላፊዎች ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ጋር ለመስራት ፍላጎት እንዳላቸው ገለፁ፡፡

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ኢቭጌኒ ተርኪን በተገኙበት በሩሲያ የኖቭግሮድ ግዛት ቀዳሚ ምክትል ገዢና አስተዳዳሪ ቦግዳኖቭ ኢቭጌኒ ከተመራ ልዑክ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይቱም ዋና ስራ አስፈፃሚው ኮርፖሬሽኑ የሚያከናውናቸውን ኢንቨስትመንት ተኮር ዝርዝር ተግባራት ለልዑኩ ያብራሩ ሲሆን÷ ኢትዮጵያና ሩሲያ ያላቸውን ፅኑ ግንኙነት በኢንቨስትመንት ለማጠናከር እንደሀገር ከፍተኛ ፍላጎት መኖሩን አስረድተዋል።

የልዑክ ቡድኑ መሪ ቦድጋኖቭ ኢቭጌኒ÷ በኖቭጎሮድ ግዛት የሚገኙ ኢንዱስትሪዎችና አምራቾች ወደ ኢትዮጵያ እንዲመጡ ለማድረግ እንደሚሰሩ ተናግዋል።

ልዑኩ ከኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ ጋር ካደረገው ውይይት በተጨማሪ የቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክን አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴ መጎብኘቱን ከኮርፖሬሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.