Fana: At a Speed of Life!

በሞስኮ በተፈፀመ ጥቃት የ60 ሰዎች ሕይወት አለፈ

 

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሩሲያ መዲና ሞስኮ በሙዚቃ ኮንሰርት አዳራሽ በተፈፀመ የጅምላ ተኩስ በርካቶች መገደላቸው እና መቁሰላቸው ተሰምቷል፡፡

በጥቃቱ እስካሁን የ60 ሰዎች ሕይወት ያለፈ ሲሆን÷ ከ100 በላይ የሚሆኑት ደግሞ መቁሰላቸው ነው የተገለፀው፡፡

ጥቃቱ በሞስኮ ሰሜን ምዕራብ አቅጣጫ በምትገኘው ኮርከስ ከተማ የተፈፀመ መሆኑን እና ጥቃቱን የፈፀሙት ታጣቂዎች አለመታወቃቸውም ተገልጿል፡፡

ጥቃት አድራሾቹ በካርከስ ከተማ በሚገኘው የኮንሰርት አዳራሽ ውስጥ በመግባት በአካባቢው በሚገኙ ጎብኚዎች ላይ ኢላማ በማድረግ የጅምላ ተኩስ መክፈታቸቸ የተገለፀ ሲሆን÷ በተጨማሪም ኮንሰርቱ የተካሄደበትን ህንፃ አቃጥለዋል፡፡

ራሺያን ታይምስ እንዳስነበበው ታጣቂዎቹ የታገተ ሰው ለማስለቀቅ ወይም ሌላ አላማ ይዘው ወደ ከተማዋ አልገቡም ይልቁኑ ሰለማዊ ዜጎችን መግደል አላማቸው ነበር ብለዋል፡፡

የሩሲያ ባለስልጣናት ድርጊቱ የሽብር ጥቃት ሊሆን እንደሚችል ጠቅሰው በጉዳዩ ላይ ምርመራ እየተደረገ መሆኑን አመላክተዋል፡፡
ለጥቃቱ እስካሁን ሃላፊነት የወሰደ አለመኖሩ ተገልጿል፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.