Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ የመጀመሪያው “የኒውክለር ሜዲሲን ማዕከል” ተከፈተ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የመጀመሪያው “የኒውክለር ሜዲሲን ማዕከል” ተከፍቷል፡፡

ማዕከሉ በፓዮኒር ዲያግኖስቲክስ ማዕከልና ረዳት ሄልዝ ኬር ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር በተባሉ ተቋማት ነው የጀመረው።

ማዕከሉ ለዚሁ አገልግሎት የሚወጣውን ከፍተኛ ወጪ በመቀነስና የውጭ ምንዛሪን በማስቀረት ረገድ ከፍተኛ ሚና አለው ተብሏል።

በመክፈቻ ስነ ስርዓቱ የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ÷ የጤና ሽፋን አገልግሎት ተደራሽነት በመንግስት አቅም ብቻ የማይሸፈን በመሆኑ የግል ዘርፉ ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን አመልክተዋል።

የግል ዘርፉ በጤና አገልግሎት ረገድ ያለው ሚና ከፍተኛ መሆኑን ጠቅሰው፤ “በዛሬው ዕለት የተከፈተው የኒውክሌር የሕክምና ማዕከል አንዱ ማሳያ ነው” ብለዋል።

መንግሥት ሶስት “የኒውክሌር የህክምና ማዕከል” ለመገንባት ከወዲሁ ቅድመ ዝግጅት አተጠናቆ ወደ ተግባር መግባቱንም አንስተዋል።

በዛሬው ዕለት የተከፈተው “የኒውክሌር ህክምና ማዕከል” የህክምና ቱሪዝም የሚያድግበትን አስቻይ ሁኔታ የሚፈጥር እንደሆነ ተገልጿል።

ማዕከሉ የላቀ የምርመራና የሕክምና አቅም እንዲሁም በኢትዮጵያ የጤና አጠባበቅ ለውጥን ያመጣል ተብሎ ተስፋ ተጥሎበታል ተብሏል።

በታሪኩ ወ/ሰንበት

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.