Fana: At a Speed of Life!

የደቡብ ኮሪያ ተሽከርካሪዎችን ለአፍሪካ ገበያ ለማቅረብ የኢትዮጵያ ስትራቴጂያዊ ፋይዳ የጎላ መሆኑ ተገለፀ

 

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ኮሪያ ተሽከርካሪዎችን ለአፍሪካ ገበያ ለማቅረብ የኢትዮጵያ ስትራቴጂያዊ ፋይዳ የጎላ መሆኑን የደቡብ ኮሪያዋ የኢንዱስትሪ ከተማ ኡልሳን ከንቲባ ዱ ጊዮም ተናገሩ፡፡

በደቡብ ኮሪያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ደሴ ዳልኬ ከደቡብ ኮሪያዋ የኢንዱስትሪ ከተማ ኡልሳን ከንቲባ ዱ ጊዮም ጋር ተወያይተዋል፡፡

አምባሳደር ደሴ ኡልሳን ከተማ ከኢትዮጵያ ከተሞች ጋር በኢንቨስትመንት ዘርፍ እንዲጠናከር ጠይቀዋል።

የደቡብ ኮሪያ ሁነኛ የማምረቻ እና የኢንዱስትሪ ከተማ በሆነችው ኡልሳን የሚገኙ ኩባንያዎች ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት በተለያዩ የኢንቨስትመንት አማራጮች እንዲሳተፉ ጥሪ በማድረግ ከንቲባውም እንዲያበረታቷቸው ጠይቀዋል።

ከንቲባ ዱ ጊዮም በበኩላቸው÷ የደቡብ ኮሪያ ተሽከርካሪዎችን ለአፍሪካ ገበያ ለማቅረብ የኢትዮጵያ ስትራቴጂያዊ ፋይዳ የጎላ ነው ብለዋል።

በቀጣይም በከተማዋ የሚገኙ ኩባንያዎች ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት በኢንቨስትመንት ላይ እንዲሠማሩ ድጋፍ ይደረጋል ማለታቸውን ከኤምባሲው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.