Fana: At a Speed of Life!

የመንግሥታቱ ድርጅት እስራኤልና ሃማስ ተኩስ እንዲያቆሙ ጥሪ አቀረበ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በጋዛ የሰብዓዊ ድጋፍ ለማቅረብ እንዲቻል እስራኤል እና ሃማስ ተኩስ እንዲያቆሙ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጥሪ አቀረበ፡፡

የድርጅቱ ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ባሳለፍነው ቅዳሜ የእስራኤልና ሃማስን ጦርነት ሸሽተው ከግማሽ በላይ የጋዛ ሕዝብ የሚገኝበትን በራፋህ ከተማ አቅራቢያ የሚገኝ ስፍራ መጎብኘታቸው ይታወሳል፡፡

በሥፍራው የሚደርስ ጥቃትም በአካባቢው ለሚገኙ ሰዎች ሁኔታዎችን የከፋ እንደሚያደርግባቸው አንስተዋል፡፡

በመሆኑም በአካባቢው ውጥረት እንዲነግስ በማድረግ ሰብዓዊ ድጋፍ እንዳይቀርብ ማድረግ ተገቢ አይደለም ሲሉ በአጽንኦት ገልጸዋል፡፡

እንደ አርቲ ዘገባ ዋና ጸሐፊው ይህን ያሉት በተመድ የፀጥታው ምክር ቤት በአሜሪካ የቀረበው አስቸኳይና ዘላቂ የተኩስ አቁም ረቂቅ የመፍትሔ ሐሳብ ውድቅ መሆኑን ተከትሎ ነው፡፡

የመፍትሔ ሐሳቡ ውድቅ ከተደረገ በኋላም እስራኤል በራፋህ የምታደርገው ዘመቻ 250 ሺህ ሰዎችን ለሞት ሊዳርግ እንደሚችል ምዕራባውያን ለተመድ አስረድተዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.