Fana: At a Speed of Life!

የመንግሥታቱ ድርጅት ያጸደቀው የጋዛ የተኩስ አቁም ውሳኔ ዓለም አቀፍ ይሁንታ አገኘ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) በጋዛ የተኩስ አቁም እንዲደረግ ያቀረበው የውሳኔ ሐሳብ በተለያዩ ሀገራት መሪዎች ተቀባይነት አገኘ፡፡

በውሳኔ ሐሳቡ ላይ በነበረው ውይይት 14 ሀገራት በጋዛ የተኩስ አቁም እንዲደረግ ተመድ ያቀረበውን ጥሪ ድምጽ በመስጠት ሲደግፉ አሜሪካ በድምፀ ተአቅቦ አልፋዋለች፡፡

በጋዛ ጦርነት ከጀተመረ አንስቶ የመንግሥታቱ ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት አስቸኳይ የተኩስ አቁም የውሳኔ ሐሳብ ሲያፀድቅ ይህ የመጀመሪያው መሆኑም ተመላክቷል፡፡

የተመድ ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ በበኩላቸው የውሳኔ ሐሳቡ ተግባራዊ ሊደረግ እንደሚገባ በአጽንኦት መግለጻቸውን አልጀዚራ ዘግቧል፡፡

ሰሞኑን እስራኤል በሰነዘረችው የአየር ጥቃት በማዕከላዊ ጋዛ ዴር ኤል ባላህ አካባቢ ቢያንስ የ22 ሰዎች በደቡብ ራፋህም የ30 ፍልስጤማውያን ሕይወት ማለፉን ዘገባው አመላክቷል፡፡

የእስራኤል ሃማስ ጦርነት ከጀመረበት ከፈረንጆቹ ጥቅምት 7 ቀን 2023 ጀምሮ ቢያንስ 32 ሺህ 333 ፍልስጤማውያን ሲሞቱ÷ 74 ሺህ 694 ደግሞ ጉዳት እንደደረሰባቸው ተመላክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.