Fana: At a Speed of Life!

ኢንዱስትሪዎች የሚያጋጥማቸውን ተግዳሮት ለመቅረፍ ይሠራል- አቶ መላኩ አለበል

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አምራች ኢንዱስትሪዎች የሚያጋጥማቸውን ተግዳሮት ለመቅረፍ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እንደሚሰራ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል ገለጹ፡፡

ሚኒስትሩ የሳፋሪ ተሽከርካሪ የምርት ሂደት ያለበትን ደረጃ ጎብኝተዋል፡፡

በጉብኝቱ ወቅትም÷ ከምርት ሂደቱ ጋር በተያያዘ አብዛኛው የሜካኒካል ሥራዎች መሠራታቸው ተገልጿል፡፡

በቀሪ ጊዜያት የምርቱን ጥራትና ደረጃ በጠበቀ መልኩ ማጠናቀቅ የሚያስችል ሥራ እየተሰራ ነው መባሉንም የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

አምራች ኢንዱስትሪዎች የሚያጋጥማቸውን ተግዳሮት ለመቅረፍም ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እንደሚሰራ ሚኒስትሩ አረጋግጠዋል፡፡

የሀገር ውስጥ አምራቾችን ለማበረታታ እና ለሀገር ውስጥ ምርቶች ቅድሚያ ለመስጠት በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት÷ በአውቶሞቲቭ ዘርፍ የሳፋሪ ተሽከርካሪዎችን ለማምረት ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው ተብሏል፡፡

ይህም የቴክኖሎጂ ሽግግርን በማስፋት፣ የተኪ ምርት ስትራቴጂን እውን በማድረግ፣ ለቱሪዝም ዘርፉ ምቹ ሁኔታዎችን በመፍጠር፣ ለዜጎች ዘላቂ የሥራ ዕድል በመፍጠር እና የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ግቦችን በማሳካት ረገድ ትልቅ ሚና እንዳለው ነው የተመላከተው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.