Fana: At a Speed of Life!

የኬንያ አየር መንገድ ከፈረንጆቹ 2017 ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ማትረፉን ገለጸ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፍሪካ ካሉት ትላልቅ አየር መንገዶች መካከል አንዱ የሆነው የኬንያ አየር መንገድ ከፈረንጆቹ 2017 ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ትርፍ ማግኘቱን ገልጿል፡፡

የአየር መንገዱ ሊቀመንበር ማይክል ጆሴፍ በፈረንጆቹ 2023 የተገኘው 80 ሚሊየን ዶላር ትርፍ ለአየር መንገዱ “ትልቅ ምዕራፍ” ነው ሲሉ መግለጻቸው ተነግሯል፡፡

የስኬቱ ዋነኛ ምክንያትም የገቢ ግብር ከ50 በመቶ በላይ መሆኑን ጠቅሰው፤ ይህም ለተሳፋሪዎች ቁጥር መጨመር መንስዔ መሆኑን ተናግረዋል።

በከፊል በመንግስት ባለቤትነት የተያዘው የኬንያ አየር መንገድ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በከፍተኛ ዕዳ ውስጥ በመዘፈቁ ችግር ውስጥ እንደገባና በኮቪድ ወረርሽኝ ወቅትም ከባድ ፈተና ገጥሞት እንደነበር ተጠቁሟል።

በፈረንጆቹ 2023 የተገኘው ውጤት አየር መንገዱ በዓመቱ አስደናቂ አፈጻጸም እንዲኖረው ማስቻሉን ጠቅሰው፤ ይህንን ለመድገምም በአየር ትራንስፖርት ዘርፍ ውስጥ አበረታች ምልክቶች እንዳሉ ያሳያል ሲሉ ሊቀመንበሩ መናገራቸውን ኤኤፍፒ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.