Fana: At a Speed of Life!

የህዳሴ ግድብ በሱዳን እና ግብፅ ከሚገኙ ግድቦች የተሻለ ድህንነት አለው- የሱዳን የመስኖና ውሃ ሚኒስትር

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 1 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በቅርቡ የውሃ ሙሌቱ የሚጀምረው የታላቁ የህዳሴ ግድብ በሱዳን እና ግብፅ ከሚገኙ ግድቦች የተሻለ ደህንነት እንዳለው የሱዳን የመስኖና ውሃ ሚኒስትር ያሲር አባስ ገለፁ።

ሚኒስትሩ ግድቡ ያረፈበት ስፍራ ለሱዳን ካለው ቅርበት ጠቀሜታ እንዳለውም አንስተዋል።

ከግድቡ ጋር በተያያዘ በተካሄዱ የተወሰኑ ጥናቶች መሰረት የህዳሴው ግድብ የደህንነት ደረጃው በበሱዳን ከሚገኝ ግድብ እና ከግብፅ ከፍተኛ ግድቦች አንፃር የተሻለ ነው ብለዋል።

ሱዳን ከራሷ ጥቅም ጋር ብቻ ትቆማለች ያሉት ሚኒስትሩ አንዳንድ ጥቅሞች ከኢትዮጵያ እና ግብፅ ጋር ይጣጣማሉ ብለዋል።

የህዳሴው ግድብ ለሱዳን ጠቃሚ ነው ስንል ከኢትዮጵያ ጋር ወግናችኋል የሚል ወቀሳ ይቀርብብናል ነው ያሉት።

ምንጭ፡-ሚዲልኢስት ሞኒተር

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.