Fana: At a Speed of Life!

ከንቲባ አዳነች በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የመኖሪያ ቤት ህንጻዎች ግንባታን አስጀመሩ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ 3 ባለ 5 ወለል የመኖሪያ ቤት ህንጻዎች ግንባታን አስጀመሩ፡፡

ከንቲባ አዳነች ዛሬ ማለዳ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ለቡ አካባቢ ለልማት ከሚኖሩበት አካባቢ ለተነሱ ነዋሪዎች፣ ለአቅመ ደካሞች እና ለሀገር ባለውለታዎች የሚሆኑ ሶስት ባለ አምስት ወለል የመኖሪያ ቤት ህንጻዎችን ግንባታ ማስጀመራቸውን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስታውቀዋል፡፡

የግንባታ ስራው ባለሃብቶችን በማስተባበር የሚሰራ ሲሆን በ90 ቀናት ውስጥ ተጠናቅቀው ለነዋሪዎች የሚተላለፉ እንደሚተላለፉ ተገልጿል፡፡

የመኖሪያ ቤቶቹ በአጠቃላይ 108 አባወራዎችን የቤት ባለቤት የሚያደርጉ እንደሚሆኑም ከንቲባ አዳነች ገልጸዋል፡፡

ለግንባታ ስራው ድጋፍ ላደረጉ ባለሃብቶችም ከንቲባዋ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.