Fana: At a Speed of Life!

የሆቴሎች ኮከብ ደረጃ ምዝና ውጤት ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የቱሪዝም ሚኒስቴር የዓለም ቱሪዝም ድርጅት ያስቀመጣቸውን አስገዳጅ መስፈርት ላሟሉ 31 ሆቴሎች የኮኮብ ደረጃ ምደባ ውጤታቸውን ይፋ አድርጓል::

በ2014 እና 2015 ዓ/ም ምዘና ከተደረገላቸው 64 ሆቴሎች መካከል ሰባቱ ባለአራት ኮኮብነት ደረጃ የተሰጣቸው ሲሆን ፥ ዘጠኝ ሆቴሎች ደግሞ የሦስት ኮከብ ደረጃን አግኝተዋል ተብሏል፡፡

አምስት ሆቴሎች የሁለት ኮከብ እና ሥምንት ሆቴሎች ባለአንድ ኮኮብነት ደረጃ የተሰጣቸው ሲሆን ፥ ሁለት ሆቴሎች ደግሞ ከደረጃ በታች መሆናቸውም ተነግሯል፡፡

እነዚህ ሆቴሎች በአዲስ አበባ፣ ቢሾፍቱ እና አዳማ ከተሞች የሚገኙ መሆኑም ነው የተገለጸው፡፡

የቱሪዝም ሚኒስትር አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ ፥ የደረጃ ምደባው ሆቴሎች ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ብቃት እንዲኖራቸው እንደሚያደርግ አንስተዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም በቅርበት ካሉ ተፎካካሪ ሀገራት ጋር ያላቸውን አቅም በማሳየት ተወዳዳሪ እንዲሆኑ እንደሚያደርጋቸው መግለጻቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.