Fana: At a Speed of Life!

በደቡብ አፍሪካ የ45 ሰዎች ሕይወት ካለፈበት አደጋ የ8 ዓመት ልጅ በሕይወት ተገኘች

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ አፍሪካ የ45 ሰዎችን ሕይወት ከቀጠፈው የተሽከርካሪ አደጋ የስምንት ዓመት ልጅ በሕይወት መገኘቷ ተሰምቷል፡፡

ከቦትስዋና ዋና ከተማ ጋቦሮኔ ወደ ሞሪያ ከተማ ሲጓዝ የነበረ አውቶቡስ ተገልብጦ የ45 ሰዎች ሕይወት ማለፉን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

አደጋው የተከሰተው አውቶቡሱ 50 ሜትር ከፍታ ካለው ድልድይ ተገልብጦ ሲሆን÷ በርካቶችን ከቀጠፈው አደጋም የስምንት ዓመት ልጅ ከባድ ጉዳት ቢደርስባትም በሕይወት ልትገኝ ችላለች።

አደጋው የተከሰተው በሰሜን ምስራቅ ሊምፖፖ ግዛት ሲሆን÷ አውቶቡስ ከድልድዩ ወደ ታች ከተገለበጠ በኋላ ከመሬት ጋር ሲጋጭ በእሳት መቀጣጠሉን ዘገባው አመላክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.