Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ በኢትዮጵያ የሩዋንዳ አምባሳደር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ በኢትዮጵያ የሩዋንዳ አምባሳደር ከሆኑት ጄን ቻርልስ ካራምባን ጋር ተወያዩ፡፡

በውይይታቸውም÷ በሁለትዮሽ፣ በቀጣናዊ ጉዳዮች እና ከአሁን በፊት ሁለቱ ሀገራት በትብብር የሚሰሩባቸውን ጉዳዮች ይበልጥ አጠናክሮ መቀጠል በሚቻልበት ዙሪያ መክረዋል።

በተጨማሪም÷ ሁለቱ ወገኖች በቀጣይ በአዲስ አበባ እና ኪጋሊ ከተሞች ያለውን እህትማማችነት የበለጠ በሚጠናከርበቱ ሁኔታ ላይም መወያየታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.