Fana: At a Speed of Life!

በጋምቤላ ክልል አንድነትን ለማሻከር የሚሠሩትን በማጋለጥ ሕብረተሰቡ ትብብሩን እንዲያጠናክር ተጠየቀ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በጋምቤላ ክልል የሕዝብን አንድነት ለማሻከር የሚሠሩ ጽንፈኛ ኃይሎችን አጋልጦ ለመንግሥት በመስጠት ረገድ ሕብረተሰቡ ትብብሩን እንዲያጠናክር የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ጥሪ አቀረበ።

የኮሚሽኑ ወንጀል መከላከል ዘርፍ ኃላፊ ምክትል ኮሚሽነር ጄኔራል መላኩ ፈንታ ከጋምቤላ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ኡሞድ ኡጁሉ ጋር በክልሉ ወቅታዊ የፀጥታ ሁኔታ ላይ ተወያይተዋል።

በውይይታቸውም የዜጎች በሰላም የመኖር ዋስትናና የሕግ የበላይነት ለድርድር የማይቀርብ የመንግሥት ኃላፊነት መሆኑን ምክትል ኮሚሽነር ጄነራል መላኩ በአጽንኦት ገልጸዋል፡፡

በክልሉ የተከሰተውን የሰላም መደፍረስ ለማረጋጋትና የዜጎችን የሰላም ዋስትና ለማረጋገጥ የጸጥታ አካላት የተለያዩ ተግባራትን እያከናወኑ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡

የሰዎችን ሰላማዊ እንቅስቃሴ የሚያደናቅፉ ችግሮች አስቸኳይ መፍትሄ እንደሚያስፈልጋቸው ማሳሰባቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ አመላክቷል፡፡

በክልሉ ሰላም እንዳይኖር፣ የሰው ሕይወት እንዲጠፋ፣ ንብረት እንዲወድምና የዜጎች ሰላማዊ እንቅስቃሴ እንዲገደብ በሚያደርጉ አካላት ላይም አስቸካይ ሕጋዊ እርምጃ ሊወሰድ ይገባል ብለዋል፡፡

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ በበኩላቸው፤ መንግሥት ሕግን ለማስከበርና የዜጎችን ሠላም ለማስጠበቅ ከመቼውም ጊዜ በላይ ቁርጠኛ መሆኑን ገልጸዋል።

ሕገ ወጥ ተግባራት ላይ የሚሳተፉ አካላት ከድርጊታቸው የማይቆጠቡ ከሆነ መንግሥት ሕግን ከማስከበር ወደ ኋላ እንደማይልም አስረድተዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.