Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያና ደቡብ ኮሪያ የ10 ሚሊየን ዶላር የድጋፍ ስምምነት አደረጉ

 

 

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ እና ደቡብ ኮሪያ የግብርና ወጪ ምርትን ለማበረታታት የሚያስችል የ10 ሚሊየን ዶላር የድጋፍ ስምምነት አድርገዋል፡፡

ደቡብ ኮሪያ በኮሪያ አለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ (ኮይካ) አማካኝነት ያደረገችው ድጋፍ በተመረጡ ዘርፎች ላይ ማለትም ቡና፣ ቅመማ ቅመም፣ ሻይ ቅጠል፣ የቅባት እህል፣ ፍራፍሬ እና የወተት ተዋጽኦ ምርቶች ላይ የሚውል ይሆናል ተብሏል፡፡

ኮይካ ከያዛቸው ፕሮጀክቶች ውስጥ የግብርና ምርቶችን የጥራት ቁጥጥር ደረጃዎችን ማሻሻል አንዱ ሲሆን÷ በዚህም የኢትዮጵያን ብሔራዊ የጥራት መሠረተ ልማት አገልግሎት ዓለም አቀፍ ዕውቅና ለማግኘት ያለመ ነው፡፡

እንዲሁም የወጪ ንግድ ገቢን ማሳደግ፣ተኪ ምርቶችን መጨመር፣ ከደረጃ በታች የሆኑ ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን ለመቀነስና የማኑፋክቸሪንግ ምርትን በጠቅላላ ሀገራዊ ምርት ላይ ያለውን ድርሻ ለማሻሻል ያለመ መሆኑን ከንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በብሔራዊ የጥራት መሠረተ ልማት ዘርፍ ላይ ለሚሰሩ ስራዎች መሻሻል የሚደረጉ የቴክኖሎጂና የገንዘብ ድጋፎች ሚናቸው የላቀ መሆኑም ተገልጿል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.