Fana: At a Speed of Life!

ኮርፖሬሽኑ ዘመናዊ የመሬት መረጃ አያያዝን ተግባራዊ አደረገ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዘመናዊ የመሬት መረጃ አያያዝ ስርዓትን በዛሬው እለት በይፋ አስጀምሯል።

የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ ፕሮግራሙን በይፋ ሲያስጀምሩ የኮርፖሬሽኑ ከፍተኛ አመራሮች፣ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ኃላፊዎች እንዲሁም በፕሮጀክቱ ተሳታፊ የነበሩ አካላት ተገኝተዋል።

ዘመናዊ የመሬት መረጃ አያያዝ ስርዓት ኮርፖሬሽኑ በዲጂታላይዜሽን ዘርፍ የጀመረው ሪፎርም ውጤታማነትን የሚያሳይ ነው ያሉት አቶ አክሊሉ፤ ለአተገባበርና ስኬታማነት ሁሉም ኢንዱስትሪ ፓርኮች እንዲሁም የመሬትና መሰረተ ልማት ዘርፍ አመራሮችና ሰራተኞች ጠንክረው መስራት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

የመሬት መረጃ አያያዝ ስርዓቱ በኮርፖሬሽኑ የሚተዳደሩ መሬቶችን ጠቅላላ መረጃ ዲጂታላይዝ በሆነ መንገድ ለመያዝ እንደሚያስችል መገለጹን ከኮርፖሬሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

በተጨማሪም የሊዝ እና የኪራይ መረጃዎችን በዘመናዊ ስርዓት በአግባቡ መዝግቦ ለመያዝ፣ ሪፖርት ለመቀበል እና ከመሬት ጋር ተያይዞ ያለውን አጠቃላይ እንቅስቃሴ በዲጂታል መንገድ ማከናወን የሚያስችል መሆኑ ተመላክቷል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.