Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አዳማ ከተማ ቅዱስ ጊዮርጊስን አሸነፈ

 

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በድሬዳዋ ስታዲየም በተካሄደው 19ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አዳማ ከተማ ቅዱስ ጊዮርጊስን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸነፈ።

10፡00 ላይ በተካሄደው ጨዋታ አዳማ ከተማ ሙሴ ኪሮስ በ6ኛው ደቂቃ እና ቢኒያም አይተን በ54ኛው ደቂቃ ባስቆጠሯቸው ጎሎች አሸንፎ ወጥቷል።

ቅዱስ ጊዮርጊስን ከሽንፈት ያላዳነችውን ጎል ታምራት እያሱ በ77ኛው ደቂቃ ላይ አስቆጥሯል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.