Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አዳማ ከተማ ቅዱስ ጊዮርጊስን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በድሬዳዋ ስታዲየም በተካሄደው 19ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አዳማ ከተማ ቅዱስ ጊዮርጊስን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸነፈ።

10፡00 ላይ በተካሄደው ጨዋታ አዳማ ከተማ ሙሴ ኪሮስ በ6ኛው ደቂቃ እና ቢኒያም አይተን በ54ኛው ደቂቃ ባስቆጠሯቸው ጎሎች አሸንፎ ወጥቷል።

ቅዱስ ጊዮርጊስን ከሽንፈት ያላዳነችውን ጎል ታምራት እያሱ በ77ኛው ደቂቃ ላይ አስቆጥሯል።

በተያያዘ ከምሽቱ 1:00 ላይ በድሬዳዋ ስታዲየም በተካሄደ የሊጉ 19ኛ ሳምንት ጨዋታ ሀዲያ ሆሳዕና ሀምበሪቾን 2 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል።

ለሀዲያ የማሸነፊያ ጎሎቹን በ64ኛው ደቂቃ ተመስገን ብርሃኑ እንዲሁም በ87ኛው ደቂቃ ዳዋ ሁጤሳ አስቆጥረዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.