Fana: At a Speed of Life!

አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ከዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት የኢትዮጵያ ተጠሪ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 1 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የዓለም አቀፍ የፍልሰተኞች ድርጅት የኢትዮጵያ ተጠሪ ማውሪን አቼንግ ጋር ተወያዩ።

አቶ ገዱ ዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት ለኢትዮጵያ እያደረገ ያለውን ድጋፍ በተመለከተ ምስጋና አቅርበው ድጋፉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ያላችውን እምነትም ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ የተቀበለቻቸውን ስደተኞች መብት በማስከበር ሙሉ ተጠቃሚ ለማድረግ በቁርጠኝነት እየሰራች መሆኑንም አንስተዋል።

የዓለም አቀፍ የፍልሰተኞች ድርጅት የኢትዮጵያ ተጠሪ ማውሪን አቼንግ በበኩላቸው ኢትዮጵያ ስደተኞችን በመቀበል እያደረገች ላለው ሁሉን አቀፍ ድጋፍ በዓለም አቀፉ ፍልሰተኞች ድርጅት ስም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

የኢትዮጵያ መንግስት ለስራቸው መሳካት እያደረገ ስላለው አገልግሎትና ሁሉን አቀፍ ድጋፍም አመስግነዋል።

ድርጅታቸው ከኢትዮጵያ ጋር የሚያደርገውን ትብብር አጠናክሮ እንደሚቀጥል ማነገራቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.