Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ የዓለም ሀገር አቋራጭ አትሌቲክስ ሻምፒዮናን በሁለተኝነት አጠናቀቀች

 

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ 45ኛውን የዓለም ሀገር አቋራጭ አትሌቲክስ ሻምፒዮናን ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቅቃለች፡፡

45ኛው የዓለም ሀገር አቋራጭ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ዛሬ ከእኩለ ቀን ጀምሮ በሰርቢያ ቤልግሬድ ተካሂዷል፡፡

ኢትዮጵያም በተለያዩ ኪሎ ሜትር ውድድሮች የተሳተፈች ሲሆን 2 ወርቅ፣6 ብር እና 2 ነሃስ በድምሩ 10 ሜዳሊያዎችን በማግኘት ሁለተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቅቃለች፡፡

በወጣት ሴቶች የ6 ኪሎ ሜትር ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከአንድ እስከ ሶስት በመውጣት አሸንፈዋል፤በተመሳሳይ በወጣት ወንዶች 8 ኪሎ ሜትር ውድድር የብር ሜዳልያ አግኝታለች፡፡

እንዲሁም በድብልቅ ሪሌ 8 ኪሎ ሜትር ውድድር የብር ሜዳሊያ ስታገኝ በአዋቂ ሴቶች 10 ኪሎ ሜትር ውድድር ግን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል አልቀናቸውም፡፡

በውድድሩ ከ51 ሀገራት የተውጣጡ አትሌቶች÷ በወጣቶች እና በአዋቂ በአምስት የውድድር ዘርፎች ተሳትፈዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.