Fana: At a Speed of Life!

ዛሬ ምሽት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የሳምንቱን ተጠባቂ ጨዋታ ያስተናግዳል

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ዛሬ ምሽት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የሳምንቱን ተጠባቂ ጨዋታ ያስተናግዳል።

የሊጉ 30ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ዛሬ ምሽት ቀጥለው ሲካሄዱ መሪዎቹ በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ ደረጃን የያዙት ክለቦች የሚያካሂዱት ጨዋታ ይጠበቃል።

ሊጉን 64 ነጥብ በመያዝ እየመራ የሚገኘው አርሴናል 63 ነጥብ በመያዝ ሶስተኛ ደረጃ ላይ ከሚገኘው ማንቸስተር ሲቲ ጋር ምሽት 12:30 ላይ ከሜዳው ውጪ ይገናኛሉ።

ከአርሴናል እኩል 64 ነጥብ ያለውና በግብ ክፍያ ተበልጦ በሊጉ ሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ሊቨርፑል በሜዳው በሊጉ ዘጠነኛ ደረጃ ላይ ከሚገኘው ብራይተን ሆቭ አልቢዮን ጋር ይጫወታል።

ትናንት በተካሄዱ የሊጉ ጨዋታ ኒውካስል ዩናይት ዌስትሃም ዩናይትድን 4 ለ 3፣ በርንማውዝ ኤቨርተንን 2 ለ 1፣ ቶተንሃም ሆትስፐር ሉተን ታውንን 2 ለ 1፣ አስቶን ቪላ ዎልቨርሃምፕተን ዎንደረርስን 2 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፈዋል።

እንዲሁም ብሬንትፎርድ ከማንቸስተር ዩናይትድ 1 ለ 1፣ ኖቲንግሃም ፎረስት ከክሪስታል ፓላስ 1 ለ 1፣ ቼልሲ ከበርንሌይ 2 ለ 2፣ ሼፊልድ ዩናይት ከፉልሃም 3 ለ 3 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.