Fana: At a Speed of Life!

በ45ኛው የዓለም ሀገር አቋራጭ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ለተሳተፉ አትሌቶች አቀባበል ተደረገ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሰርቢያ ቤልግሬድ በተካሄደው 45ኛው የዓለም ሀገር አቋራጭ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ለተሳተፉ አትሌቶች በቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ደማቅ አቀባበል ተደረጎላቸዋል፡፡

የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር መስፍን ቸርነትና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ረዳት ኮሚሽነር አትሌት ደራርቱ ቱሉ ለአትሌቲክስ ቡድኑ አቀባበል አድርገዋል።

በተጨማሪም የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ እና ሌሎችም የፌዴሬሽን አመራሮች በመገኘት ለአትሌቶቹ አቀባበል እንዳደረጉላቸው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን መረጃ ያመላክታል።

በሰርቢያ ቤልግሬድ በተካሄደው የ45ኛው የዓለም ሀገር አቋራጭ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ በ14 ሴት እና በ14 ወንድ በ28 አትሌቶች የተወከለች ሲሆን፥ በሁለት ወርቅ፣ በስድስት ብር እና በሁለት ነሃስ በአጠቃላይ በ10 ሜዳሊያ ከዓለም የሁለተኛነት ደረጃ በመያዝ ውድድሩርን ማጠናቀቋን ይታወቃል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.