Fana: At a Speed of Life!

በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ማስታወሻነት የተዘጋጀ ቴምብር ተመረቀ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ማስታወሻነት የተዘጋጀ ቴምብር ተመረቀ፡፡

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ፕሮጀክት የመሰረት ድንጋይ የተጣለበት 13ኛ ዓመት በዓል “በኅብረት ችለናል” በሚል መሪ ሐሳብ በአዲስ አበባ እየተከበረ ነው።

በአከባበሩ ላይ የተገኙት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን የ13 ዓመታትን ጉዞ የሚያሳይ የስዕልና የፎቶ ዐውደ-ርዕይ መርቀዋል፡፡

እንዲሁም በኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት የተዘጋጀ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ማስታወሻ ቴምብር መመረቁን የውኃና ኢነርጂ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.