Fana: At a Speed of Life!

ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ ከጃፓን መንግስት የተበረከተላትን የኒሻን ሽልማት ተረከበች

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ ከጃፓን መንግስት የተበረከተላትን የወርቅ ጨረር ያለው የኒሻን ሽልማት ተረክባለች።

ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ በስፖርት ዲፕሎማሲ ላበረከተችው አስተዋፅኦ ቀደም ሲል ከጃፓን መንግስት የክብር ኒሻን ሽልማት የተበረከተላት መሆኑ ይታወሳል፡፡

በጃፓን እና በኢትዮጵያ መካከል ካበረከተችው የስፖርት ዲፕሎማሲ በተጨማሪ ለአትሌቲክስ እድገት እና ለሀገር ሰላም ላበረከተችው አስተዋፅኦም ነው ሽልማቱ የተበረከተላት፡፡

በዚህም በኢትዮጵያና ጃፓን የሁለትዮሽ ግንኙነት ታሪክ ከኢትዮጵያ የወርቅ ጨረር ያለው የኒሻን ሽልማት ያገኘች የመጀመሪያዋ ኢትዮጵያዊ መሆን ችላለች፡፡

ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ ሽልማቷን ከኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር ሺባታ ሂሮኖሪ መረከቧንም የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.