Fana: At a Speed of Life!

ክርስቲያኖ ሮናልዶ በክለቦች ብቻ የሰራው ሀትሪክ 55 ደረሰ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአልናስሩ የፊት መስመር ተጫዋች ክርስቲያኖ ሮናልዶ በክለቦች ውስጥ ባለው የእግርኳስ ሕይወት በአንድ ጨዋታ ላይ ሶስት ጎሎችን በማስቆጠር (ሃትሪክ) ያለውን ታሪክ 55 አድርሷል።

ትናንት ምሽት በሳኡዲ ፕሮ ሊግ አል ናስር አብሃን 8 ለ 0 በሆነ ውጤት ባሸነፈበት ጨዋታ ሮናልዶ ከእረፍት በፊት ሶስት ጎሎችን በማስቆጠር ሃትሪክ ሰርቷል፡፡

በዚህም የ39 ዓመቱ አጥቂ በክለብ ያስቆጠራቸውን የሶስታ (ሃትሪክ) ቁጥር ወደ 55 ከፍ ያደረገ ሲሆን በአጠቃላይ በብሔራዊ ቡድን ያስቆጠራቸውን ጨምሮ በእግርኳስ ዘመኑ 65 ሃትሪክ መስራት ችሏል፡፡

ተጫዋቹ በእግርኳስ ዘመኑ በስምንት ጨዋታዎች 4 ጎሎችን፣ በሁለት ጨዋታዎች 5 ጎሎችን በ45 ጨዋታዎች ደግሞ ሶስት ጎሎችን ማስቆጠር ችሏል፡፡

ከክርስቲያኖ ሮናልዶ በመቀጠል ብዞ ሃትሪክ በመስራት ረገድም ሊዮኔል አንድሬስ ሜሲ 53 የክለብ ሃትሪክ በመስራት ስሙ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ በ48 ጨዋታዎች 3 ጎሎችን፣ በአምስት ጨዋታዎች 4 ጎል እንዲሁም በአንድ ጨዋታ ደግሞ 5 ጎሎችን ማስቆጠር ችሏል፡፡

የኡራጓዩ አጥቂ ሉዊስ ስዋሬዝ 29 ሃትሪክ በመስራት ሶስተኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠ ተጫዋች ሲሆን፤ በ20 ጨዋታዎች ሶስት ጎሎችን፣ በ8 ጨዋታዎች 4 ጎሎችን እንዲሁም በ1 ጨዋታ 6 ጎሎችን ማስቆጠር ችሏል፡፡

ሮቤርቶ ሌዋንዶውስኪ በ22፣ ሰርጂዮ አጉዌሮ በ17፣ ኤድሰን ካቫኒ በ15 እንዲሁም ራዳሜል ፋልካው በ12 ጨዋታዎች ሃትሪክ የሰሩ ተጫዋቾች ናቸው፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.