Fana: At a Speed of Life!

ዳያስፖራውን በኢንቨስትመንት ዘርፎች ተሳታፊ በሚያደርግ ማዕቀፍ ላይ ውይይት እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ዳያስፖራውን በተለያዩ የኢንቨስትመንት አማራጮች ተሳታፊ በሚያደርግ ማዕቀፍ ዙሪያ በባሕርዳር ከተማ ውይይት እየተካሄደ ነው።

የውይይት መድረኩ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት ከአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዳያስፖራ ጉዳዮች አማካሪ ጋር በመተባበር ነው የተዘጋጀው፡፡

የአማራ ክልል የርዕሰ መስተዳድሩ ዳያስፖራ ጉዳዮች አማካሪ አቶ አላዩ መኮንን÷ ዳያስፖራውን ተሳታፊ ማድረግ የሚያስችል ማዕቀፍ አስፈላጊነትን በተመለከተ ለውይይት ተሳታፊዎች ገለጻ አድርገዋል።

በኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት የተዘጋጀው መነሻ ማዕቀፉ ዳያስፖራው በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች፣ በመኖሪያ ቤት ልማትና በሌሎች የልማት አማራጮች ተሳታፊ እንዲሆኑ የሚያደርግ ነው ተብሏል።

በውጭ ሀገራት የሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያንን ከሀገራቸው ጋር በልማት በማስተሳሰር ለኢትዮጵያ ልማትና እድገት የራሳቸውን አሻራ እንዲያኖሩ የሚያስችል መሆኑም ተገልጿል።

ጠቋሚ ማዕቀፉ ዳያስፖራውን አንድ የልማት አቅም አድርጎ ለመጠቀም ምቹ ሁኔታዎችን መፍጠር ላይ ታሳቢ ያደረገ መሆኑንም የርዕሰ መስተዳድሩ ጽ/ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

አሁን ላይም በአገልግሎቱ የተዘጋጀው ጠቋሚ ማዕቀፉ በኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት የዳያስፖራ ማሕበረሰብ ልማት ተሳትፎ ዳይሬክተር ነብዩ ሰለሞን ቀርቦ ውይይት እየተደረገበት ይገኛል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.