Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ የረመዳን ወርን ምክንያት በማድረግ ለ127 ሺህ በላይ ነዋሪዎች ማዕድ የማጋራት መርሃ ግብር ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የረመዳን ወር ጾምን ምክንያት በማድረግ ከ127 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ነዋሪዎች ማዕድ የማጋራት መርሃ ግብር ማስጀመሩን የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።

ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት÷ “በለውጡ መንግስት በጀመርነው የሰው ተኮር ስራችን የህዝባችንን የኑሮ ጫና የማቅለልና አለኝታነታችንን በተግባር የማረጋገጥ በርካታ ስራ በመስራት፣ ማዕድ ብቻ ሳይሆን ለወገኖቻችን ክብር እና ፍቅርን እያጋራን ቆይተናል” ብለዋል።

በዛሬው ዕለትም ለሁሉም የአዲስ አበባ መስጅዶች የሚከፋፈል ቴምር እና ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ ወገኖች ደግሞ ማዕድ ማጋራታቸውን በመልዕክታቸው ገልጸዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.